በጌዲዮ ገደብ እና ቀርጫ መጠለያ ጣቢያ ያሉትን ተፈናቃዮች ጉብኝት

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በዛሬው ዕለት ቃል በገባው መሰረት በጌዲዮ ገደብ እና ቀርጫ መጠለያ ጣቢያ ያሉትን ተፈናቃዮች ፕሬዚዳንቱ ታማኝ በየነን ጨምሮ ለዚሁ ዓላማ ከተለያየ ስቴት የመጡ ሦስት የቦርድ አባላት ያሉበት ቡድን ጉብኝት አድርጓል። እግረመንገድም በጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮችን በሁለቱም ዞኖች መልሶ ለማቋቋም ከማህበሩ ጋር ባለፈው ሮብ ውል ካሰረው ወርልድ ቪዥን ጋር በመሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል። ምንጭ:- ክብሬ ተስፋዬ ከግሎባል አለያንስ ድጋፍ ስጭ ኮሚቴ አባል አ/አ

Tsehay Demeke